ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱ የበኵራት በለስ ፍሬ ናቸው፤ በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።
በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።
አንዱ ቅርጫት፣ ቶሎ የደረሰ ፍሬ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፣ በሌላው ቅርጫት ግን ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበላ የማይቻል እጅግ መጥፎ በለስ ነበረበት።
ነገሥታትን ይንቃል፤ በገዦችም ላይ ያፌዛል፤ በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤ የዐፈር ቍልል ሠርቶም ይይዘዋል።
የበለስ ዛፍ በብርቱ ነፋስ ስትወዛወዝ ያልበሰለው ፍሬ ከርሷ እንደሚረግፍ፣ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።