የወንዙ በር ወለል ብሎ ተከፈተ፤ ቤተ መንግሥቱም ወደቀ።
ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤ ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤ ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤ መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ።
ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣ አስቀድሞ ተነግሯል፤ ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤ ደረታቸውንም ይደቃሉ።
እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ ሁሉም ሴቶች ናቸው! የምድርሽ በሮች፣ ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቷቸዋል።