“ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ? ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው? እስኪ መልስልኝ!
“ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ ልንገርህ፤ እስራኤል ሆይ፤ በአንተ ላይ ልመስክር፤ አምላክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በቃልህ ትጸድቅ፣ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ፣ አንተን፣ በርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፉ ነገር አደረግሁ።
“ምነው ሕዝቤ ቢያደምጠኝ ኖሮ፣ እስራኤል በመንገዴ በሄደ ኖሮ፣
“ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤ እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ!
ከዚህ ካደረግሁለት በላይ ለወይኔ ቦታ ምን ሊደረግለት ይገባ ነበር? መልካም የወይን ፍሬ ያፈራል ብዬ ስጠብቅ ለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?
“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤ “እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤ ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣ ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣ ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?
ሕዝቤ ሆይ፤ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣ የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስኪ አስቡ፤ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣ ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን ዐስቡ።”
እንግዲህ አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለም በሙሉ ለእግዚአብሔር መልስ እንዲሰጥ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደ ሆነ፣ እናውቃለን፤