“ስለዚህ ሰማርያን የፍርስራሽ ክምር፣ ወይን የሚተከልባትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ አወርዳለሁ፤ መሠረቷንም ባዶ አደርጋለሁ።
ከአንዲቱ ከተማ ቢገባ፣ እስራኤል ሁሉ ገመድ አምጥቶ አንድ ድንጋይ እንኳ እስከማይቀር ድረስ፣ ከተማዪቱን ወደ ሸለቆ ስበን እንከታታለን።”
በሦስተኛውም ዓመት መጨረሻ ያዛት። ሰማርያ የተያዘችውም ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት፣ ሆሴዕ በእስራኤል ላይ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ነበር።
ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ የእስራኤልም ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ወደ ሰማርያ ገሥግሦ ከተማዪቱን ከበባት፤
“ ‘ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት፣ አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣ አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
ስለ ደማስቆ የተነገረ ንግር፤ “እነሆ፤ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማነቷ ይቀራል፤ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።
ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤ ወደ ታች ያወርደዋል፤ ወደ ምድር አውርዶም ትቢያ ላይ ይጥለዋል።
ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤ የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤ የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤ ተመልሳም አትሠራም።
እንደ ገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ፣ ወይን ትተክያለሽ፤ አትክልተኞች ይተክሏቸዋል፤ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል።
“አንቺ ምድርን ሁሉ ያጠፋሽ፣ አጥፊ ተራራ ሆይ፤ እኔ በአንቺ ላይ ነኝ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ከገመገም ቍልቍል አንከባልልሻለሁ፤ የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።
ባቢሎን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮዎች መፈንጫ፣ የድንጋጤና የመሣለቂያ ምልክት ትሆናለች፤ የሚኖርባትም አይገኝም።
“ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ጐሬ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች፣ ሰው የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።
በኖራ የለሰናችሁትን ካብ አፈርሳለሁ፤ መሠረቱም ተገልጦ እስኪታይ ድረስ ከምድር ጋራ አደባልቀዋለሁ። ቅጥሩ በሚወድቅበት ጊዜ፣ እናንተም በውስጡ ታልቃላችሁ። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
የሰማርያ ሰዎች በደላቸውን ይሸከማሉ፤ በአምላካቸው ላይ ዐምፀዋልና። በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ሕፃኖቻቸውም በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤ የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።”
እናንተ ድኻውን ትረግጣላችሁ፤ እህል እንዲሰጣችሁም ታስገድዱታላችሁ፤ ስለዚህ በተጠረበ ድንጋይ ቤት ብትሠሩም፣ በውስጡ ግን አትኖሩም፤ ባማሩ የወይን ተክል ቦታዎች ወይን ብትተክሉም፣ የወይን ጠጁን ግን አትጠጡም፤
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዳዋ የወረሰው ጕብታ ይሆናል።
ሕዝብህን ለመታደግ፣ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የክፋትን ምድር መሪ ቀጠቀጥህ፤ ከራስ ጠጕሩ እስከ እግር ጥፍሩም ዕርቃኑን አስቀረኸው። ሴላ
እርሱ ግን፣ “ይህን ሁሉ ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተክቦ የምታዩት፣ ሳይፈርስ እንዲሁ እንዳለ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ አይኖርም” አላቸው።