ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው፤ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።
ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚባል ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ።
ዮሴፍም ሥጋውን ወስዶ በንጹሕ የበፍታ ጨርቅ ከፈነው፤