Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ማቴዎስ 26:14

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ በኋላ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባለው ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀነናዊው ስምዖንና በኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።

አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም፣ “መምህር ሆይ፣ እኔ እሆንን?” አለው። እርሱም፣ “አንተ አልህ” አለው።

በመናገር ላይ እያለ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ዘንድ የተላኩ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎችም ዐብረውት ነበሩ።

አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፤ የወሰደውን ሠላሳ ጥሬ ብር ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ ሽማግሌዎች መልሶ በመስጠት፣

ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ ኋላ አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ግን በመቃወም እንዲህ አለ፤

እራትም ቀርቦ ሳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ የስምዖንን ልጅ የአስቆሮቱን ይሁዳ ልብ አነሣሥቶ ነበር።

ኢየሱስም፣ “ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።

ይሁዳም ያን ቍራሽ እንጀራ እንደ ተቀበለ ወጥቶ ሄደ፤ ሌሊትም ነበረ።

ብዙውን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በዚያ ስለሚገናኝ፣ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ቦታውን ያውቅ ነበር።

እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፣ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፉ ቃል መፈጸም ስላለበት፣

ይህ ሰው ስለ ክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በዚያም በግንባሩ ተደፍቶ ሰውነቱ እመካከሉ ላይ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች