ይህ ሁሉ ግን የምጡ መጀመሪያ ነው።
ከእስረኞች ጋራ ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋራ ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤ የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
“ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ሰዎች ያስሯችኋል፤ ያሳድዷችኋል፤ ወደ ምኵራቦችና ወደ ወህኒ ቤት ያስገቧችኋል፤ በነገሥታትና በገዦች ፊት ለፍርድ ያቀርቧችኋል፤ ይህም ሁሉ በስሜ ምክንያት ይደርስባችኋል።
እግዚአብሔር አስፈሪ መቅሠፍት፣ አስጨናቂና ለብዙ ጊዜ የሚቈይ መዓት፣ አሠቃቂና በቀላሉ የማይወገድ ደዌ በአንተና በዘሮችህ ላይ ይልክባችኋል።
ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።
እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስሙ፤ ስለሚደርስባችሁ መከራ አልቅሱ፤ ዋይ ዋይም በሉ።