ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይመነጫል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው፤
ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል።
የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤ የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው።
የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤ የሞኞች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል።
የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤ የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።
ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።
ምናምንቴና ጨካኝ ሰው፣ ነውረኛ አንደበቱን ይዞ የሚዞር፣
እናንተ የእፉኝት ልጆች፤ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ መልካም ነገር መናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ የሞላውን አንደበት ይናገረዋልና።
ሰውን የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው እንጂ ወደ አፉ የሚገባው አይደለም።”
በአፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ ዘልቆ፣ ከዚያም ወደ ውጭ እንደሚወጣ አታውቁምን?
ቀጥሎም፣ እንዲህ አለ፤ “ከሰው የሚወጣ ያ ሰውን ያረክሰዋል፤
“ጌታውም እንዲህ አለው፤ ‘አንተ ክፉ ባሪያ! በራስህ ቃል እፈርድብሃለሁ፤ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፣ ያልዘራሁትን የማጭድ፣ ጨካኝ ሰው መሆኔን ካወቅህ፣
በጥንት አባባል፣ ‘ከክፉ አድራጊዎች ክፉ ድርጊት ይወጣል’ እንደ ተባለ፤ አሁንም እጄ በአንተ ላይ አትሆንም።