ፈሪሳውያንም ይህን አይተው፣ “እነሆ፣ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን እያደረጉ ነው” አሉት።
“ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ በቤትህ የተወለደው ባሪያና መጻተኛው ያርፉ ዘንድ በሰባተኛው ቀን ምንም አትሥራ።
ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የሰንበት ዕረፍት፣ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ በዕለቱ ማንኛውንም ዐይነት ሥራ የሚሠራ ቢኖር ሞት ይገባዋል።
“እግሮችህ ሰንበትን እንዳይሽሩ ብታሳርፍ፣ በተቀደሰው ቀኔ የልብህን ባታደርግ፣ ሰንበትን ደስታ፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን የተከበረ ብለህ ብትጠራው፣ በገዛ መንገድህ ከመሄድ፣ እንደ ፈቃድህ ከማድረግና ከከንቱ ንግግር ብትቈጠብ፣
በዚያም አንድ እጁ ሽባ የሆነ ሰው ነበር፤ ኢየሱስን ሊከስሱት ምክንያት ፈልገው፣ “በሰንበት ቀን መፈወስ ተፈቅዷል?” ብለው ጠየቁት።
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ዳዊትና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ፣ እርሱ ምን እንዳደረገ አላነበባችሁምን?
ፈሪሳውያንም፣ “እነሆ፤ በሰንበት ቀን ለምን ያልተፈቀደውን ነገር ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት።
ኢየሱስም ሕግ ዐዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን፣ “በሰንበት ቀን ሕመምተኞችን መፈወስ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?” ሲል ጠየቃቸው፤
ከዚያም ተመልሰው ሽቱና ቅባት አዘጋጁ፤ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት በሰንበት ቀን ዐረፉ።
ከፈሪሳውያን መካከል አንዳንዶቹ ግን፣ “በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን ለምን ታደርጋላችሁ?” አሏቸው።