ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤
ከዚያም ሰሎሞን ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። እናቱ ናዓማ የተባለች አሞናዊት ነበረች። ልጁ አብያም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
ሮብዓም መንግሥቱን ከመሠረተና ካጸና በኋላ፣ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ።
የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ገና ሕፃን ሳለ፣ ምንም ማድረግ በማይችልበትና እነርሱንም ለመቋቋም ዐቅሙ በማይፈቅድለት ጊዜ የማይረቡ ምናምንቴዎች በዙሪያው ተሰበሰቡበት፣ በረቱበትም።
ከዚያም ሰሎሞን ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ቀበሩት። ልጁም ሮብዓም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
አሣፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥ ይሆራምን ወለደ፤ ይሆራም ዖዝያንን ወለደ፤
በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን፣ ከአብያ የክህነት ምድብ የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ነገድ ስትሆን፣ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ።