በዐመፃ ተነሣሥተው ነፍስ ከገደሉ ዐመፀኞች ጋራ የታሰረ በርባን የሚባል አንድ ሰው ነበረ።
በዚያ ጊዜ በዐመፅ የታወቀ በርባን የሚባል እስረኛ ነበር።
በበዓል ሕዝቡ እንዲፈታላቸው የሚጠይቁትን እስረኛ የመልቀቅ ልማድ ነበር።
ሕዝቡም መጥተው እንደተለመደው እንዲያደርግላቸው ለመኑት።
የሕዝብ ዐመፅ በማነሣሣትና በነፍስ ግድያ ታስሮ የነበረውን፣ እንዲፈታላቸውም የለመኑትን ያን ሰው ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን እንዳሻቸው እንዲያደርጉት አሳልፎ ሰጣቸው።