በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፣ “ትንቢት ተናገር!” ይሉት ነበር። ጠባቂዎቹም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።
ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወጥቶ ሚክያስን በጥፊ መታውና፣ “ለመሆኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በየት በኩል ዐልፎኝ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።
ንጉሡ ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ሲመለስ አስቴር ደገፍ ባለችበት ድንክ ዐልጋ ላይ ሐማ ተደፍቶ ነበር። ንጉሡም፣ “ይባስ ብሎ ዐብራኝ ያለችውን ንግሥት በገዛ ቤቴ ሊደፍራት ያስባልን?” ሲል ተናገረ። ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ ገና እንደ ወጣ፣ የሐማን ፊት ሸፈኑት።
ይጸየፉኛል፣ ወደ እኔም አይቀርቡም፤ ያለ ምንም ይሉኝታ በፊቴ ይተፋሉ።
ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ ጢሜን ለሚነጩ ጕንጬን ሰጠሁ፤ ፊቴን ከውርደት፣ ከጥፋትም አልሰወርሁም።
ብዙዎች በርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣ መልኩ ከማንም ሰው ተለየ፤ ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።
በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።
አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ ከበባ ተደርጎብናልና። የእስራኤልን ገዥ፣ ጕንጩን በበትር ይመቱታል።
እግዚአብሔርም ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት።
ተፉበትም፤ የሸንበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው ራሱን መቱት፤
ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ከዚያም ይገድሉታል፤ እርሱ ግን ከሦስት ቀን በኋላ ይነሣል።”
ራሱንም በበትር መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።
ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት ጠባቂዎች አንዱ፣ “ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው እንዲህ ነውን?” ብሎ በጥፊ መታው።
እየተመላለሱም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ በጥፊ ይመቱት ነበር።
በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ በጳውሎስ አጠገብ የቆሙትን ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዘ።
የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።