አሳልፎ የሚሰጠውም፣ “እኔ የምስመው እርሱ ነውና ያዙት፤ ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት” በማለት አስቀድሞ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር።
ደሙም ያላችሁበትን ቤት ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆንላችኋል፤ እኔ ደሙን በማይበት ጊዜ እናንተን ዐልፋለሁ፤ ግብጽን ስቀጣ መቅሠፍቱ አይደርስባችሁም።
ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣ የወዳጅ ማቍሰል ይታመናል።
ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፤ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።”
ወዲያው እየተናገረ ሳለ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ዐብረውትም ሰይፍና ዱላ የያዙ፣ ከካህናት አለቆች፣ ከጸሐፍትና ከሽማግሌዎች የተላኩ ብዙ ሰዎች ነበሩ።
እንደ ደረሰም ወዲያው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ!” ብሎ ሳመው፤
ክፉኛ ከተደበደቡ በኋላም ወደ ወህኒ ቤት አስገቧቸው፤ የወህኒ ቤት ጠባቂውም ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
በማንኛውም መንገድ በተቃዋሚዎቻችሁ አትሸበሩ፤ ይህ እነርሱ እንደሚጠፉ፣ እናንተ ግን እንደምትድኑ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምልክት ነው።
ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ የመልእክቶቼም ሁሉ መለያ ይህ ነው፤ አጻጻፌም እንደዚህ ነው።
“እንግዲህ እኔ በጎነትን እንዳሳየኋችሁ ሁሉ፣ እናንተም በጎነትን ለአባቴ ቤት እንድታሳዩ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ መተማመኛ የሚሆን ምልክትም ስጡኝ፤