እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሠራ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፣ ብልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
ንጉሡ ማእዱ ላይ ሳለ፣ የእኔ ናርዶስ መዐዛውን ናኘው።
ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤ በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣ በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣ የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ።
ትቷቸው ከከተማው ወጣ፤ ወደ ቢታንያም ሄዶ በዚያው ዐደረ።
እንዲሁም ሁለት ታላንት የተቀበለው ሁለት አተረፈ፤
ሆኖም፣ “ሕዝቡ ዐመፅ እንዳያነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም” ይባባሉ ነበር።
በዚያ ከነበሩት አንዳንዶቹ በድርጊቱ ተቈጥተው እንዲህ ይባባሉ ነበር፤ “ሽቱው ለምን እንደዚህ በከንቱ ይባክናል?
ይህች ወንድሟ አልዓዛር የታመመባት ማርያም፣ ጌታን ሽቱ ቀብታ እግሮቹን በጠጕሯ ያበሰችው ነበረች።