እንደ ገናም ሌላ ባሪያ ላከ። እነርሱም ራሱን ፈንክተውና አዋርደው መለሱት።
ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው።
በርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፣ በኀጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጕራም ዐናት ይፈነካክታል።
እነርሱ ግን ይዘው ደበደቡት፤ ባዶ እጁንም ሰደዱት።
አሁንም እንደ ገና ሌላ ላከ፤ ይህኛውንም ገደሉት፤ ከሌሎች ከብዙዎቹ መካከል አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ አንዳንዶቹንም ገደሉ።
ቀጥሎም ሌላ ባሪያውን ላከ፤ ገበሬዎቹም እርሱንም ደግሞ ደበደቡት፤ አዋርደውም ባዶ እጁን ሰደዱት።