ዮሐንስ የግመል ጠጕር ይለብስ፣ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሓ ማርም ይበላ ነበር።
እነርሱም “ሰውየው ጠጕራም፣ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። ንጉሡም፣ “ዐወቅሁት፤ ቴስብያዊው ኤልያስ ነው” አላቸው።
ከእነዚህ ማንኛውንም ዐይነት አንበጣ፣ ፌንጣና ኵብኵባ መብላት ትችላላችሁ።
“በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው የትንቢት ራእይ ያፍራል፤ ለማታለልም የነቢያትን ጠጕራም ልብስ አይለብስም።
የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር።
በመላው ይሁዳ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎችም በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በርሱ እጅ ተጠመቁ።
ስብከቱም፣ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበረታው ከእኔ በኋላ ይመጣል።