ኤልያስ ከእነዚህ መካከል ወደ አንዷም አልተላከም፤ ነገር ግን በሲዶና አገር በሰራፕታ ወደ ነበረችው መበለት ተላከ።
በከነዓን ያለው ይህ የእስራኤል ስደተኞች ወገን፣ እስከ ሰራፕታ ያለውን ምድር ይወርሳል፤ በሰፋራድም ያሉ የኢየሩሳሌም ስደተኞች፣ የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።
“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን ኖሮ፣ ገና ዱሮ ማቅ ለብሰው፣ ዐመድ ነስንሰው ንስሓ በገቡ ነበር።