ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ በማእድ ከእኔ ጋራ ናት።
የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸውም በላዬ ተነሡ፤
እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።
በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ መጣ።
ኢየሱስም፣ “ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።