ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤
እስኪያፍር ድረስም፣ አዛሄልን ትኵር ብሎ ተመለከተው፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ሰው እንባውን አፈሰሰ።
ሕግህ ባለመከበሩ፤ እንባዬ እንደ ውሃ ይፈስሳል።
ቃልህን አይጠብቁምና፣ ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ።
ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣ ቍጣ ወረረኝ።
ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤ አምርሬ ላልቅስበት፣ ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣ ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።
እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣ በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።
ባትሰሙ ግን፣ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣ ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤ እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።
እረኛ ሆኜ አንተን ከማገልገል ወደ ኋላ አላልሁም፤ ክፉ ቀን እንዳልተመኘሁ ታውቃለህ፤ ከአንደበቴ የሚወጣውም በፊትህ ግልጽ ነው።
ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጕረፊያ በሆኑልኝ!
“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።
እንዲህም አለ፤ “ሰላምሽ የሚሆነውን ምነው አንቺ ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ! አሁን ግን ከዐይንሽ ተሰውሯል፤
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።