ኢየሱስም፣ “እይ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።
ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።
እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ፣ “አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው! እንደ ፈለግሽው ይሁንልሽ” አላት። ልጇም ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰች።
ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ!” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።
ኢየሱስም ወደ ኋላ ዘወር ብሎ ሴቲቱን አያትና፣ “አይዞሽ፣ ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ተፈወሰች።
ሰውየውንም፣ “ተነሥተህ ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።
“ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። ዐይነ ስውሩም፣ “ጌታ ሆይ፤ ዳግም እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው።
ኢየሱስም ሴቲቱን፣ “እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት።
እርሱም፣ “ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ ፈውሶሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት።