“እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፍግ እስከማደርግላት ድረስ ለዘንድሮ ብቻ ተዋት፤
ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር።
“አቤቱ ጌታ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ጌታ ከእኛ ጋራ ይሂድ፤ ይህ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ቢሆንም እንኳ፣ ክፋታችንንና ኀጢአታችንን ይቅር በል፤ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቢቆሙ፣ ልቤ ለዚህ ሕዝብ አይራራምና ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ!
የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ።
በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉ ካህናት፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አደባባይ መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን በአሕዛብ መካከል መተረቻ፣ መሣቂያና መሣለቂያም አታድርግ፤ ለምንስ በሕዝቦች መካከል፣ ‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ይበሉን።”
የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፣ ‘እነሆ፤ ፍሬ ለማግኘት ልፈልግባት ሦስት ዓመት ወደዚህች በለስ መጥቼ ምንም አላገኘሁም፤ ስለዚህ ቍረጣት፤ ለምን ዐፈሩን በከንቱ ታሟጥጣለች?’ አለው።
ለከርሞ ካፈራች መልካም ነው፤ አለዚያ ትቈርጣታለህ።’ ”
ለመሬትም ሆነ ለማዳበሪያነት የማይጠቅም በመሆኑ ወደ ውጭ ይጣላል። “ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።”
ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እስራኤላውያን የልቤ ምኞት፣ እግዚአብሔርንም የምለምነው እንዲድኑ ነው።
ይኸውም የገዛ ወገኖቼን እንዲቀኑ አነሣሥቼ ከእነርሱ ጥቂቱን ለማዳን ተስፋ በማድረግ ነው።
አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።