የእናንተ የራሳችሁ ጠጕር ሁሉ እንኳ የተቈጠረ ነው፤ እንግዲህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ።
እርሷም፣ “ደም ተበቃዮቹ ልጄን በማጥፋት የባሰ ጕዳት እንዳያደርሱ፣ ንጉሡ አምላኩን እግዚአብሔርን ይለምን” አለች። ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ከልጅሽ ራስ ላይ አንዲት ጠጕር እንኳ አትነካም” አላት።
ከምድር እንስሳት ይልቅ የሚያስተምረን፣ ከሰማይ ወፎችም ይልቅ ጠቢባን የሚያደርገን፣ እርሱ የት አለ?’
በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤
ታዲያ ሰው ከበግ እጅግ አይበልጥምን? ስለዚህ በሰንበት ቀን በጎ ማድረግ ተፈቅዷል” አላቸው።
እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጕር አንዷ እንኳ አትጠፋም፤
ስለዚህ፣ ለደኅንነታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጕር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።”
ሕዝቡ ግን ሳኦልን፣ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? አይደረግም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።