አባት በወንድ ልጁ ላይ፣ ወንድ ልጅም በአባቱ ላይ፣ እናት በሴት ልጇ ላይ፣ ሴት ልጅም በእናቷ ላይ፣ ዐማት በምራቷ ላይ፣ ምራትም በዐማቷ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።”
ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፣ ምራት በዐማቷ ላይ ትነሣለች፤ የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ ናቸውና።
እኔ የመጣሁት “ ‘ልጅን ከአባት፣ ሴት ልጅን ከእናቷ ምራትንም ከዐማቷ ለመለያየት ነው፤
በዚያ ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ ይጠላላሉም።
ከአሁን ጀምሮ እርስ በርስ የተለያዩ በአንድ ቤተ ሰብ ውስጥ ዐምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሁለቱ በሦስቱ ላይ፣ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።