ሙሴም ማኅበሩን፣ “እግዚአብሔር እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው” አላቸው።
ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ።
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን ወደ ፊት አወጣቸው፤ በውሃም ዐጠባቸው።