“ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፤
ከዚያም ሕዝቅያስ፣ “እነሆ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል፤ አሁንም ቅረቡ፤ መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ” አላቸው። ስለዚህ ጉባኤው መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ አመጡ፤ ልባቸው የፈቀደ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
ከዚያም የእግዚአብሔርን መሠዊያ ዐደሰ፤ በላዩም የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መሥዋዕት አቀረበ፤ ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ አዘዘ።
“በቤቴ የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ፤
እንዲሁም ውሃ ከጠገበው ከእስራኤል መሰማሪያ፣ ሁለት መቶ በግ ካለው ከእያንዳንዱ መንጋ አንድ በግ ይውሰድ። ይህ ሁሉ ለሕዝቡ ማስተስረያ ለሚሆነው ለእህል ቍርባን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለኅብረት መሥዋዕት ይውላል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
መሥዋዕቱም ባቀረባችሁት ዕለት ወይም በማግስቱ ይበላ፤ እስከ ሦስተኛው ቀን የተረፈ ማንኛውም ነገር ይቃጠል።
“ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ፣ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጋችሁ አቅርቡት።
ማንኛውም በዘይት የተለወሰ ወይም ደረቅ የእህል ቍርባን ለአሮን ልጆች ሁሉ እኩል ይሰጥ።
“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ስለ ራሱ መሥዋዕት አድርጎ ከዚሁ ላይ ለእግዚአብሔር ያቅርብ።
የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልቀበለውም፤ ከሠቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልመለከተውም።
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የሶገር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።