በዚህ ሁኔታ ኀጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣ የሰረቀውን ወይም የቀማውን ወይም በዐደራ የተሰጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን ይመልሳል፤
ከዚያም አብርሃም፣ የአቢሜሌክ አገልጋዮች ነጥቀው ስለያዙበት የውሃ ጕድጓድ መከፋቱን ለአቢሜሌክ ገለጠለት።
ዕርሻቸውን፣ የወይንና የወይራ ዘይት ተክል ቦታቸውንና ቤታቸውን በቶሎ መልሱላቸው፤ እንዲሁም የምታስከፍሏቸውን የገንዘቡን፣ የእህሉን፣ የአዲሱን ወይንና ዘይት አንድ መቶኛ ዐራጣ መልሱላቸው።”
ድኾችን በመጨቈን ባዶ አስቀርቷቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቋል።
ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤ የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።
ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑም፤ በሚሠሩትም ሰውነታቸውን መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸው ክፉ ነው፤ እጃቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞላ ነው።
ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣ በጕልበት ቢቀማ፣ በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣ አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣
አባቱ ግን የሰውን መብት ስለ ደፈረ፣ ወንድሙን በጕልበት ስለ ቀማና በሕዝቡ መካከል የማይገባውን ስላደረገ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል።
ማንንም አይጨቍንም፤ ነገር ግን በመያዣ የወሰደውን እንኳ ለተበዳሪው ይመልሳል፤ ለተራበ የራሱን እንጀራ፣ ለተራቈተም ልብስ ይሰጣል እንጂ፣ በጕልበት አይቀማም።
ለሰጠው ብድር የተቀበለውን መያዣ ቢመልስ፣ የሰረቀውንም መልሶ ቢሰጥ፣ ሕይወት የሚሰጡትን ትእዛዞች ቢከተል፣ ክፉ ነገርንም ባያደርግ፣ በርግጥ እርሱ በሕይወት ይኖራል፤ አይሞትምም።
ሕዝቡ ወዳለበት ወደ ውጩ አደባባይ ሲወጡ፣ ሲያገለግሉበት የነበረውን ልብስ አውልቀው በተቀደሱት ክፍሎች በመተው ሌሎች ልብሶችን ይልበሱ፤ ይኸውም ሕዝቡን በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ነው።
የሌላውን ሰው እንስሳ ደብድቦ የገደለ ማንኛውም ሰው ያንኑ ዐይነት እንስሳ ይተካለት።
እንስሳ የገደለ ማንኛውም ሰው በገደለው ፈንታ ይተካ፤ ሰው የገደለ ግን ይገደል።
የወይፈኑን ብልት ሁሉ ከሰፈር ውጭ ዐመድ ወደሚፈስስበት በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነው ስፍራ ይውሰደው፤ በተቈለለው ዐመድ ላይ ዕንጨት አንድዶ ያቃጥለው።
“ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣ በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።
በዚያ ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የአማልክታቸውን ቤት፣ በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።”
ደግሞም፣ ‘ይህ ድካም ነው’ በማለት በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “በቅሚያ የመጣውን፣ ዐንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ቍርባን አድርጋችሁ ስታቀርቡ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል እግዚአብሔር፤
በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ስለ በደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ ዐምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤