ዕርሻውን ባይዋጅ ወይም ለሌላ ሰው አሳልፎ ቢሸጥ፣ ከዚያ በኋላ ሊዋጀው አይችልም።
ዕርሻውን የቀደሰው ሰው መልሶ መዋጀት ከፈለገ፣ በዋጋው ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት፤ ከዚያ በኋላ ዕርሻው እንደ ገና የራሱ ይሆናል።
ዕርሻው በኢዮቤልዩ በሚለቀቅበት ጊዜ ለእግዚአብሔር እንደ ተሰጠ ዕርሻ ተቈጥሮ ቅዱስና የካህናቱ ንብረት ይሆናል።
በኢዮቤልዩ ዓመትም የዕርሻው መሬት የቀድሞው ባለርስት ለነበረው፣ ለሸጠውም ሰው ይመለሳል።