Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘሌዋውያን 27:11

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንስሳው በሥርዐቱ መሠረት የረከሰ፣ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የማይገባው ከሆነ፣ ሰውየው እንስሳውን ወደ ካህኑ ያቅርብ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰውየው መልካም የሆነውን እንስሳ መልካም ባልሆነው፣ መልካም ያልሆነውንም መልካም በሆነው አይለውጥ ወይም አይተካ፤ አንዱን እንስሳ በሌላው ከተካም ሁለቱ የተቀደሱ ይሆናሉ።

መልካም ቢሆን ወይም ባይሆን፣ ካህኑ ዋጋውን ይወስን፤ የካህኑም ውሳኔ የጸና ይሆናል።

“በመንጋው ውስጥ ተቀባይነት ያለው ተባዕት በግ ኖሮት ይህንኑ ሊሰጥ ተስሎ ሳለ፣ በማታለል ነውር ያለበትን እንስሳ ለጌታ የሚሠዋ ርጉም ይሁን፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ ሊፈራ የሚገባ ነውና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ለዝሙት ዐዳሪ ሴት ወይም ለወንደቃ የተከፈለውን ዋጋ ለማንኛውም ስእለት አድርገህ ለመስጠት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታምጣ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች