“ ‘ሥራ የምትሠሩበት ስድስት ቀን አላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው። የእግዚአብሔር ሰንበት ስለ ሆነ፣ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩበት።
እርሱም አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ‘ነገ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሰንበት በመሆን፣ የዕረፍት ቀን ይሆናል።’ ስለዚህ መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትን ቀቅሉ። የተረፈውን አስቀምጡ፤ እስከ ጧትም ድረስ አቈዩት።”
እግዚአብሔር ሰንበትን የሰጣችሁ መሆኑን ልብ በሉ፤ በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ የሰጣችሁ ለዚህ ነው። በሰባተኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ባለበት ይቈይ፤ ማንም አይወጣም።”
ስለዚህ ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ዐረፉ።
“ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ በቤትህ የተወለደው ባሪያና መጻተኛው ያርፉ ዘንድ በሰባተኛው ቀን ምንም አትሥራ።
“ስድስት ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ፤ በዕርሻና በመከር ወቅት እንኳ ቢሆን ማረፍ አለብህ።
ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣ እነዚህን የሚፈጽም ሰው ብፁዕ ነው።”
እርሱን ለማገልገል፣ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋራ ያቈራኙ መጻተኞች፣ የእግዚአብሔርን ስም በመውደድ፣ እርሱንም በማምለክ፣ ሰንበትን ሳያረክሱ የሚያከብሩትን ሁሉ፣ ቃል ኪዳኔንም የሚጠብቁትን፣
“እግሮችህ ሰንበትን እንዳይሽሩ ብታሳርፍ፣ በተቀደሰው ቀኔ የልብህን ባታደርግ፣ ሰንበትን ደስታ፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን የተከበረ ብለህ ብትጠራው፣ በገዛ መንገድህ ከመሄድ፣ እንደ ፈቃድህ ከማድረግና ከከንቱ ንግግር ብትቈጠብ፣
“ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
የምኵራቡ አለቃ ግን፣ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን፣ “ሥራ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው።
ከዚያም ተመልሰው ሽቱና ቅባት አዘጋጁ፤ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት በሰንበት ቀን ዐረፉ።
የሙሴ ሕግማ ከጥንት ጀምሮ በየሰንበቱ በምኵራብ ሲነበብና በየከተማው ሲሰበክ ኖሯልና።”
በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከበስተ ኋላዬ ሰማሁ፤