“ትእዛዞቼን ጠብቁ፤ አድርጓቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
“ ‘ሥርዐቴን ጠብቁ። “ ‘የተለያዩ እንስሳትን አታዳቅል። “ ‘በዕርሻህ ላይ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ። “ ‘ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።
“ ‘ሥርዐቴንና ሕጌን ሁሉ ጠብቁ፤ ተከተሏቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”
መሥዋዕቱ በዚያ ዕለት ይበላ፤ ለሚቀጥለውም ቀን አታሳድሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ቅዱስ መሆኔ በእስራኤላውያን ዘንድ ይታወቅ፤ የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ስለዚህ ትእዛዞቼን ሁሉ ለመፈጸም ታስባላችሁ፤ ለአምላካችሁም የተቀደሳችሁ ትሆናላችሁ።
ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለዘላለም በሚሰጥህም ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ጠብቅ።