Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘሌዋውያን 20:17

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘አንድ ሰው የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ የሆነችውን እኅቱን አግብቶ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አድራጎቱ አሳፋሪ ነው፤ በሕዝባቸው ፊት ከሕዝባቸው ተለይተው ይጥፉ። ሰውየው እኅቱን አዋርዷልና ይጠየቅበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞም እኮ በርግጥ እኅቴ ናት፤ ከአንድ እናት ባንወለድም በአባት አንድ ነን፤ ኋላም አገባኋት።

እርሷም እንዲህ አለችው፤ “እባክህ ወንድሜ ተው አይሆንም! አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አታድርግ።

ተመሳሳይ ዐይነት የሠራና ከካህናት ሌላ በማንም ሰው ላይ ያፈሰሰ ሁሉ ከወገኑ ይወገድ።’ ”

በውስጥሽ አንዱ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ ሌላውም የልጁን ሚስት ያስነውራል፤ ሌላው ደግሞ የገዛ እኅቱ የሆነችውን የአባቱን ልጅ ይደፍራል።

“ ‘ከእኅትህ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፣ ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋራ በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

“ ‘አንዲት ሴት ወደ እንስሳ ቀርባ ግብረ ሥጋ ብትፈጽም፣ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

ባልየውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ግን በበደሏ ምክንያት የሚመጣውን ፍዳ ትቀበላለች።’ ”

“የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው እኅቱ ጋራ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች