የእህል ቍርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ።
እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀርበውን ገጸ ኅብስት፣ የእህል ቍርባኑን ዱቄት፣ ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፈረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኀላፊነት የሚቈጣጠሩ እነርሱ ነበሩ።
ቈራርሰህ ዘይት አፍስስበት፤ ይህ የእህል ቍርባን ነው።
በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀውን የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር አምጥተህ ለካህኑ አስረክብ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ይወስደዋል፤
በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ፣ በመቀቀያ ወይም በምጣድ የበሰለ ማንኛውም የእህል ቍርባን ለሚያቀርበው ካህን ይሰጥ።