የእህል ቍርባንህ በምጣድ የሚጋገር ከሆነ፣ እርሾ ሳይገባበት በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ቂጣ ይሁን።
ቈራርሰህ ዘይት አፍስስበት፤ ይህ የእህል ቍርባን ነው።
በሚገባ በዘይት ተለውሶ በምጣድ ላይ ይጋገር፤ ከዚያም የእህሉን ቍርባን ቈራርሰህ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ አቅርብ።
“ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋራ ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥሡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት ዐብሮ ያቅርብ።
በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ፣ በመቀቀያ ወይም በምጣድ የበሰለ ማንኛውም የእህል ቍርባን ለሚያቀርበው ካህን ይሰጥ።
ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣