“ ‘ፍርድ አታዛቡ፤ ለድኻው አታድላለት፤ ለትልቁም ሰው ልዩ አክብሮት አትስጥ፤ ለብርቱው አታድላ፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።
ለርሱ ታደላላችሁን? ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን?
ለማንም አላደላም፤ ሰውንም አላቈላምጥም።
ሁሉም የእጁ ሥራ ስለ ሆኑ፣ እርሱ ለገዦች አያደላም፤ ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።
“ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ
ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው።
ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።
እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ምሳሌዎች ናቸው፦ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤
ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”
“ ‘በመስፈሪያ ወይም በሚዛን አታጭበርብሩ።
የሰውን ፊት በማየት መፍረድ ትታችሁ ቅን ፍርድ ፍረዱ።”
ጳውሎስም፣ “አንተ በኖራ የተለሰንህ ግድግዳ! እግዚአብሔር ደግሞ አንተን ይመታሃል፤ በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ፣ ያለ ሕግ ስላስመታኸኝ አንተ ራስህ ሕጉን ጥሰሃል” አለው።
በፍርድ አድልዎ አታድርጉ፤ ትልቁንም ትንሹንም እኩል እዩ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንኛውንም ሰው አትፍሩ። ከዐቅማችሁ በላይ የሆነውን ሁሉ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔ አየዋለሁ።”
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጕቦ አትቀበል፤ ጕቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።
“በመጻተኛው፣ አባት በሌለውና በመበለቲቱ ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።