ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።
ከዚያም በሆድ ዕቃዎች ያለውን ስብ ሁሉ፣ የጕበቱን መሸፈኛና ሁለቱንም ኵላሊቶች በዙሪያቸው ካለው ስብ ጋራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥላቸው።
ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።
“ ‘ነገር ግን እስራኤላውያን ከመንገዴ ስተው በወጡ ጊዜ፣ የመቅደሴን ሥራ በታማኝነት ያከናወኑት የሳዶቅ ዘር የሆኑት ሌዋውያን ካህናት፣ በፊቴ ቀርበው ያገለግሉኛል፤ በፊቴ ቆመው የሥብና የደም መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እስራኤላውያን የሚሠዉትን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡበት ምክንያት ይህ ነው። ይህንም ካህኑ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥተው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በማድረግ ያቅርቡ።
ካህኑም ይህን ሁሉ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።
በራሱም ላይ እጁን ይጫንበት፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።
ካህኑም ይህን ሁሉ በእሳት የሚቀርብና ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ሥብ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።
በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።
የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነድደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።
በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።
ሥቡን ከኅብረት መሥዋዕት በወጣበት አኳኋን ሥቡን ሁሉ ያውጣ፤ ካህኑም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህም መሠረት ካህኑ የሰውየውን ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።
“የተቀደሱ ስለ ሆኑ የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል በኵር የሆኑትን አትዋጃቸውም፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ሥባቸውንም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ ታቃጥለዋለህ።