“ ‘እንዲበላ የተፈቀደውን ማንኛውንም እንስሳ ወይም ወፍ ዐድኖ የያዘ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደሙን ከውስጡ ያፍስስ፤ ዐፈርም ያልብሰው፤
“ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!
ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።
“ ‘የሰው ደም በመካከሏ አለ፤ በገላጣ ዐለት ላይ አደረገችው እንጂ፣ ዐፈር ሊሸፍነው በሚችል፣ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “ከእናንተ ማንም ደም አይብላ፤ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛም ቢሆን ደም አይብላ” አልሁ።
በየትኛውም ቦታ ብትኖሩ የማንኛውንም የወፍ ዘር ወይም የእንስሳ ደም አትብሉ።
ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።
ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።