እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤
“ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።
“ለአሮንና ለልጆቹ፣ ለእስራኤላውያንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤