ካህኑም ከዘይቱ ጥቂቱን በግራ እጁ መዳፍ ውስጥ ያፍስስ፤
ለበደል መሥዋዕት የሚሆነውንም የበግ ጠቦት ይረድ፤ ካህኑም ከደሙ ጥቂት ወስዶ የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮ ታችኛ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ፤
ካህኑም የቀኝ እጁን ጣት በመዳፉ በያዘው ዘይት ውስጥ በመንከር በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ጊዜ ይርጭ።