“ ‘በባሕሮችና በወንዞች ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን መብላት ትችላላችሁ፤
ነገር ግን በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ሁሉ፣ ከሚንፏቀቁት ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ሌሎች ፍጥረታት መካከል ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ፤
የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ይሁኑ።
በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።
በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑ፣ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፤ የሚጠቅመውስ በፍቅር የሚገለጽ እምነት ብቻ ነው።
ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ሥራ አለኝ።” እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።