ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።
ግፍ ብትውሉባቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ፣ ጩኸታቸውን በርግጥ እሰማለሁ።
ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ።
የመበለቶቻቸውን ቍጥር፣ ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ፤ የጐበዛዝት እናቶች በሆኑትም ላይ፣ አጥፊውን በቀትር አመጣባቸዋለሁ። ሽብርንና ድንጋጤን፣ በድንገት አወርድባቸዋለሁ።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ ጕልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።
አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”