ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሯል፤ በራብም ተቃጥሏል።
ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ።
ጢስ የጠጣ የወይን አቍማዳ ብመስልም፣ ሥርዐትህን አልረሳሁም።
እርሱ ሥጋዬንና ቈዳዬን አስረጀ፤ ዐጥንቶቼንም ሰባበረ።
አሁን ግን ከጥላሸት ይልቅ ጠቍረዋል፤ በመንገድም የሚያውቃቸው የለም፤ ቈዳቸው ከዐጥንታቸው ጋራ ተጣብቋል፤ እንደ ዕንጨትም ደርቀዋል።