ከሁሉም በላይ በከንቱ ርዳታን ስንጠባበቅ፣ ዐይኖቻችን ደከሙ፤ ከግንብ ማማችን ላይ ሆነን፣ ሊያድን ከማይችል ሕዝብ ርዳታ ጠበቅን።
የባቢሎንም ንጉሥ ከግብጽ ደረቅ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ የነበረውን ግዛቱን ሁሉ ወስዶበት ስለ ነበር፣ የግብጽ ንጉሥ ከአገሩ ዳግም ለዘመቻ አልወጣም።
በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብጽ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም።
ከሞት ጋራ የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤ ከሲኦልም ጋራ ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤ ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ እናንተም ትጠራረጋላችሁ።
ከሺሖር ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣ አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ? ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣ ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?
መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣ ለምን ትሮጫለሽ? አሦር እንዳዋረደሽ፣ ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል።
የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣ በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያም ትወጫለሽ።
“መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።”
“ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነርሱ ግን ከዱኝ፤ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ፣ ምግብ ሲፈልጉ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ዐለቁ።
በተጨነቀችባቸውና በተንከራተተችባቸው ቀናት፣ ኢየሩሳሌም በጥንት ዘመን የነበራትን፣ ሀብት ሁሉ ታስባለች፤ ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፣ የረዳት ማንም አልነበረም፤ ጠላቶቿ ተመለከቷት፤ በመፈራረሷም ሣቁ።
እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ ለአሦርና ለግብጽ እጃችንን ሰጠን።
ግብጽ ከእንግዲህ ለእስራኤል ሕዝብ መታመኛ አትሆንም፤ ለርዳታ ወደ እርሷ ዘወር ባሉ ጊዜ ላደረጉት ኀጢአት ግን መታሰቢያ ትሆናለች። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”