እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ ፍርዴን ፍረድልኝ!
ራሔልም፣ “እግዚአብሔር ፈርዶልኛል፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ አወጣችለት።
የአባቴ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋራ ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ሰድደኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መከራዬን አይቶ፣ ልፋቴን ተመልክቶ ትናንት ሌሊት ገሠጸህ።”
አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚታገሉኝን ታገላቸው፤ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።
አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ! ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ።
አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ ካልታመኑህ ሕዝብ ጋራ ተሟገትልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።
ፍርዴም ጕዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤ ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።
ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል።
ሰው ፍትሕ ሲጓደልበት፣ ጌታ እንዲህ ዐይነቱን ነገር አያይምን?
በቀላቸውን ሁሉ፣ በእኔም ላይ ያሰቡትን ዐድማ አየህ።
ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራ ሲደርስበት አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።