“ጠላቶቻችን ሁሉ፣ አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ።
እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣ አፋቸውን ከፈቱብኝ።
እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።
ሕዝቦች፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ? የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም በቀል፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦች ይወቁት።
እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣ በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን።
በእስራኤላውያን ዘንድ ግን በሰውም ሆነ በእንስሳት ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽባቸውም።’ በዚህም እግዚአብሔር በግብጻውያንና በእስራኤላውያን መካከል ልዩነት የሚያደርግ መሆኑን ታውቃላችሁ።
ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣ አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤ ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤ እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤ የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤ ኖረንም ልናየው በቃን።”