እስራኤላውያንም አቢሜሌክ መሞቱን ሲያዩ ወደ የቤታቸው ተመለሱ።
ከዚያም ኢዮአብ ቀንደ መለከት ነፍቶ ስለ ከለከላቸው፣ ሰራዊቱ እስራኤልን ማሳደዱን አቆመ።
ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤ ጥልና ስድብም ያከትማል።
ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “ ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ።
አቢሜሌክ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል፣ በአባቱ ላይ ስላደረሰው በደል እግዚአብሔር የእጁን ከፈለው።