ከዚያም አቢሜሌክ ወደ ቴቤስ በመሄድ ከተማዪቱን ከብቦ ያዛት።
የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”
ከዚያም ዖምሪና ዐብረውት ያሉት እስራኤላውያን ሁሉ ከገባቶን ወደ ላይ ወጥተው ቴርሳን ከበቡ።
ሰዎቹም ሁሉ ቅርንጫፎች ቈርጠው አቢሜሌክን ተከተሉት፤ ቅርንጫፎቹንም ምሽጉ ላይ አስደግፈው በመከመር ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ በእሳት አቃጠሏቸው። ስለዚህ በሴኬም ግንብ ውስጥ የነበሩት አንድ ሺሕ ያህል ወንዶችና ሴቶች ሞቱ።
ሆኖም በከተማዪቱ ውስጥ ብርቱ ግንብ ስለ ነበር፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማዪቱ ገዦችም ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በውስጥ ዘግተው ወደ ግንቡ ጣራ ወጡ።