ገዓል የሴኬምን ገዦች መርቶ በመውጣት አቢሜሌክን ተዋጋው፤
ከዚያም ዜቡል፣ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልሀቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።
ሆኖም አቢሜሌክ አሳደደው፤ እስከ መግቢያው በር ድረስ ባለው መንገድ ሲሸሹም ብዙ ሰዎች ቈስለው ወደቁ።