የአቤድ ልጅ ገዓል ከከተማዪቱ ወጥቶ በመግቢያው በር ላይ ሲቆም፣ አቢሜሌክና ሰዎቹ ካደፈጡበት ወጡ።
በዚህ ጊዜ የአቤድ ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋራ ወደ ሴኬም መጣ፤ የሴኬምም ገዦች ተማመኑበት።
ስለዚህ አቢሜሌክና ሰዎቹ በሙሉ በሌሊት ወጡ፤ በአራት ምድብ ሆነውም በሴኬም አጠገብ አደፈጡ።
ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፣ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ” ነው አለው።