Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መሳፍንት 8:5

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሱኮትንም ሰዎች፣ “የምድያምንም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን በማሳደድ ላይ ስለ ሆንሁ የተከተሉኝም ሰዎች ስለ ደከሙብኝ እባካችሁ የሚበሉትን እንጀራ ስጧቸው” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የልዑል አምላክ ካህን የነበረው የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤

ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።

እግዚአብሔር ከመቅደሱ ተናገረ፤ “ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፋፍላለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።

ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጕዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖር ልጅ በለዓምን አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት።

የእግዚአብሔር መልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’ ‘ሕዝቧንም ዐብራችሁ ርገሙ፤ ከኀያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት፣ በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ።

በዚህ ጊዜ ዛብሄልና ስልማና ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ከሆነ ሰራዊታቸው ጋራ ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺሕ ሰይፍ ታጣቂ ሰራዊት የተረፈው ነበር።

ሁለቱ የምድያም ነገሥታት ዛብሄልና ስልማና ሸሹ፤ ጌዴዎን ግን አሳድዶ ያዛቸው፤ መላ ሰራዊታቸውንም እጅግ በታተነው።

ከዚያም ጌዴዎን ወደ ሱኮት ሰዎች መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ ‘ለደከሙት ሰዎችህ እንጀራ እንሰጥ ዘንድ ዛብሄልና ስልማና በእጅህ ገብተዋልን’ በማለት ያላገጣችሁብኝ ዛብሄልና ስልማና እነዚሁላችሁ።”

አቢግያም ጊዜ አላጠፋችም፤ ሁለት መቶ እንጀራ፣ ሁለት አቍማዳ የወይን ጠጅ፣ ዐምስት የተሰናዱ በጎች፣ ዐምስት መስፈሪያ የተጠበሰጠ እሸት፣ መቶ የወይን ዘለላና ዘቢብ፣ ሁለት መቶ ጥፍጥፍ የበለስ ፍሬ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች