ከዚህ በኋላ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሐሬስ መተላለፊያ በኩል አድርጎ ከጦርነቱ ተመለሰ፤
ሁለቱ የምድያም ነገሥታት ዛብሄልና ስልማና ሸሹ፤ ጌዴዎን ግን አሳድዶ ያዛቸው፤ መላ ሰራዊታቸውንም እጅግ በታተነው።
እርሱም የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ማረከ፤ መረመረውም፤ ወጣቱም የሰባ ሰባት የሱኮት ሹማምትና የከተማዪቱንም አለቆች ስም ጻፈለት።